አዲስ አበባ | ጥቅምት 14፤ 2016|- ትውልደ ኢትዮጵያ ታዳጊ ሄማን በቀለ የቆዳ ካንሰርን የሚከላከል ሳሙና በመስራት 9 ተወዳዳሪዎች ጋር በመፎካከር 25 ሺህ ዶላር የሚያሸልም ውድድርን አሸንፏል፡፡

ታዳጊ ሄማን በቀለ “የአሜሪካ ወጣት ምርጥ ተመራማሪ” የሚል ክብር የተቀዳጀ ሲሆን “የቆዳ ካንሰር በአብዛኛው በታዳጊ ሀገራት የሚገኙ ዜጎች ላይ ነው የሚከሰተው” የሚለው ታዳጊው፥ በ0 ነጥብ 05 ዶላር ለገበያ የሚውሉ ሳሙናዎችን ሰርቷል፡፡
ወጣቱ የተሸለመውን 25 ሺህ ዶላር የፈጠራ ስራውን በስሙ ለማስመዝገብና ወደ ኮሌጅ ሲገባ ምርምሩን ለመቀጠል እንደሚጠቀምበት ገልጿል።
እንደ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ በ2028 የሳሙና ምርቶቹን በታዳጊ ሀገራት በነጻ የሚያከፋፍል ግብረሰናይ ድርጅት ለማቋቋም ማቀዱን ገልጿል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv