አዲስ አበባ | ጥቅምት 12 2016| NBC ETHIOPIA – ???? በቅርቡ እድሜያቸው ከ45 ዓመት በላይ በሆኑ 26,000 የካናዳ ዜጎች ላይ ለ3 ዓመት በተደረገ ጥናት በብዛት የእንቅልፍ እጦት ችግር የሚታይባቸው ግለሰቦች ከፍተኛ የሆነ የመዘንጋት ችግር ታይቶባቸዋል ብሏል።

???? እነዚህ ግለሰቦች ለመዘንጋት ችግር ተጋላጭ የሚያደርጉ እንደ ድብርት፣ ጭንቀት፣ ውፍረትና በእንቅልፍ ጊዜ የአተነፋፈስ ችግር በብዛት እንደነበረባቸው ታውቋል። በተጨማሪም ከሴቶች አንፃር ወንዶች ለዚህ ችግር ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናቱ አረጋግጧል።
???? የእንቅልፍ እጦት (Insomnia) ህመም ሆኖ ህክምና የሚሰጠው አንድ ግለሰብ በአማካኝ በሳምንት ለ3ቀን ያህል እንቅልፍ ለመተኛት ሲቸገርና ደጋግሞ ከእንቅልፉ ሲነቃ ይህም ከ3 ወር በላይ ከዘለቀና የቀን ተቀን ተግባሩን ማከናወን ሲከለክለው ነው።
???? ነገር ግን የእንቅልፍ እጦት ችግር በጊዜ ከታወቀና ህክምና ከተደረገለት በቀላሉ መታከም የሚችልና እንደ ዲመንሻያ ያሉ የማይድኑ ህመሞችን ከማስከተሉ በፊት መከላከል የሚቻል በሽታ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












