አዲስ አበባ | ጥቅምት 12 2016| NBC ETHIOPIA – የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና አጋር ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ከጥቅምት 14-16 የሚያካሂዱት ጉባኤው በኢትዮጵያ ላሉ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች እና ኢንተርፕርነሮች ምቹ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል።

በተጨማሪም ሀገሪቱ በፈጠራ ዘርፍ እድገት እንድታመጣ እንደሚያግዛት ተስፋ ተጥሎበታል።
ከ80 በላይ ስታርትአፕና ስራ ፈጣሪዎች፣ ሚኒስቴሮች፣ አምባሳደሮች፣ ባለድርሻ አካላት የጉባኤው ተሳታፊ እንደሚሆኑ የሚጠበቅ ሲሆን አሸናፊ ስታርትአፖች ተሸላሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም ሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የስራ ፈጠራ ምህዳሩን ለማጎልበት ያለመ “Next Ethiopian Startup Initiative (NEST) የተሰኘ መርሃ ግብር ጥቅምት 13 2016 ዓ.ም ለማካሄድ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።
ሁለቱን ዝግጅቶች በተመለከተ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












