አዲስ አበባ | ጥቅምት 08 2016| NBC ETHIOPIA – አንዳንዴ ሰምተን ከሆነ መጋኛ መታው፣መጋኛ ፊቱን አጣመመው ሲባል ሰምተን ሊሆን ይችላል የዚህን ነገር ሳይንሳዊ ትርጉሜ ይዘንላችሁ ቀርበናል።

-ፊታችን ከጭንቅላታችን በሚነሱ ነርቮች አማካኝነት የእለት ተእለት ተግባራትን ይከውናል። ከጭንቅላታችን የሚነሱ 12 የጭንቅላት ነርቮች (cranial nerves) አሉ። ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ነርቮች የፊታችንን እንቅስቃሴ ያዛሉ፣ ይቆጣጠራሉ። ፊታችን ቀስ በቀስ ወይም በድንገት ሊጣመም ይችላል።
-ድንገተኛ የሆነ የፊት መጣመም የምንለው በአንድ በኩል የሚገኘውን የፊት ጡንቻዎች መድከም ፣ መስነፍ ወይም መዛል ሲሆን የፊታችንን ቅርፅ የሚቀይር ከአንጎል ከሚነሱት 12 ነርቮች አንዱ የሆነው ሰባተኛው ነርቭ (facial nerve) እብጠት ምክንያት የሚመጣ የነርቭ ህመም ነው።
-ይህ ችግር በማንኛውም የእድሜ ክልል ሊከሰት የሚችል ፣ ግማሽ ፊታችን ወይ በቀኝ ወይም በግራ ፊት እንዳይታዘዝ የሚያደርግ ህመም ነው ።
-ይህም ፊታችንን የሚመግቡ ነርቮች (nerve supplies) ከጭንቅላታችን ሲወጡ በሚከሰት ጫና ወይም ጉዳት ሊከሰት ይችላል።
ምክንያቶቹስ ምንድን ናቸው?

-ይህ ነው የሚባል ምክንያት ባይቀመጥም አንዳንድ ኤክስፐርቶች በአንድ በኩል የሚገኘውን የፊታችንን ጡንቻ የሚቆጣጠረው ነርቭ ሲቆጣ ፣ ወይም እብጠት ሲኖረው ነው ብለው አሰቀምጠዋል።
-ይህም በተለይ በቫይረስ ኢንፌክሽን አማካኝነት ነው ተብሎ ይታሰባል። እነዚህ ቫይረሶች ለምሳሌ Herpes simplex virus,herpes zosther, episten barr virus, CMV virus, mumps virus, adeno virus ይጠቀሳሉ።
ተጋላጭ ሰዎችስ እነማን ናቸው?

-ነፍሰጡር እናቶች ፣ የላይኛው የመተንፈሻ አካል ኢንፌክሽን ፣ ስኳር ፣ ደም ግፊት እና ከመጠን በላይ ውፍረት ያለባቸው ሰዎች ፣ ተጋላጭ ናቸው ተብሎ ይታሰባል።
ምልክቶቹስ?
-በአብዛኛው ጊዜ ምልክቶቹ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በተወሰነ መልኩ ይመለሳል ተብሎ ይታሰባል። ሙሉ ለሙሉ ወደ ነበረበት ለመመለስ ሳምንታትን ወይም ወራት ሊፈጅ ይችላል።
የተወሰኑ ሰዎች ላይ ደግሞ እስከ ህይወት ዘመን ሊቆይ ይችላል።
-ድንገተኛ የሆነ በአንድ በኩል ብቻ የፊት መድከም ፣ መስነፍ ፣ የፊት መውደቅ ፣ ጉንጭ በአየር መሙላት መቸገር ፣ መሳቅ ፣ ፈገግ ማለት ፣ እና ሌሎች የፊት እንቅስቃሴዎች ለማድረግ መቸገር ፣ የፊት መደንዘዝ ፣ አንድ ዓይንን መክደን አለመቻል ፣ የምራቅ መዝረክረክ ፣ ማፏጨት አለመቻል ፣ የአፍ በአንድ በኩል መውረድ ፣ በግንባር መኮሳተር አለመቻል ፣ ከጆሮ ጀርባ አና መንጋጭላ አካባቢ የህመም ስሜት ፣ ራስ ምታት፣ ጣእም ለማጣጣም መቸገር ፣ የእንባ እና የምራቅ መጠን መለወጥ ፣ ሊኖሩ ይችላሉ።
የሚያመጠውስ መዘዝ?

-የፊት ነርቭ በቋሚነት መጎዳት
-የነርቭ ዘንጎች በትክክል አለማደግ
-የዓይን መድረቅ ፣ የዓይን ኢንፌክሽን ፣ መታወር ድረስ ሊያስከትል ይችላል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












