አዲስ አበባ | መስከረም 7 2016| NBC ETHIOPIA – ቻይና ከፍተኛ ዲፕሎማቷን ዋንግ ዪን በደህንነት ጉዳይ ላይ ውይይት ለማድረግ ወደ ሩሲያ ልካለች፡፡ ሞስኮ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጦርነት ለመቀጠል ድጋፍ እንደምትፈልግም በዚህ የሁለትዮሽ ውይይት ወቅት የሚነሳ ጉዳይ ይሆናል ተብሏል።

የሞስኮ የቅርብ ወዳጅ የሆነችው ቤጂንግ ፤ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ወቅት ሩሲያን በተዘዋዋሪ ትደግፋለች የሚል ክስ ከምዕራባውያን ቢቀርብባትም ቻይና ግን ይሄን ውንጀላ አትቀበልም።
የ ዋንግ ጉዞ ቭላድሚር ፑቲን በቅርቡ ወደ ቤጂንግ ጉብኝት እንዲያደርጉ መንገድ ይከፍታል ተብሎም ይታሰባል።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ፑቲን ከቻይና ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር እንደሚገናኙ ገልፀው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ትክክለኛውን ቀን ግን አልገለፁም።
ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በዩክሬን ጦርነት ወቅት የጦር ወንጀሎችን ፈፅመዋል በሚል የእስር ማዘዣ ካወጣ በኋላ ወደ ፑቲን ውጭ ሀገር ሄደው እንደማያውቁ ቢቢሲ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












