አዲስ አበባ | መስከረም 4 2016| NBC ETHIOPIA-የእንግሊዙ ክለብ ኤቨርተን ለአሜሪካው 777 የኢንቨስትመንት ኩባንያ ተሸጠ።

ላለፉት 7 አመታት ክለቡን በባለቤትነት ሲያስተዳድሩ የቆዩት ፋርሃድ ሞሽሪ 94 በመቶ ድርሻውን መሸጣቸው ተረጋግጧል።
የሊጉ የእግር ኳስ ማህበር እና የፋይናንስ ባለስልጣን ሽያጩን ካጸደቀ በኋላ የርክክብ ሂደቱ በ2023 መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል ተብሏል።በምን ያህል ሂሳብ ስለመሸጡ የተገለጸ ነገር የለም።
የአሜሪካው 777 የኢንቨስትመንት ኩባንያ ኤቨርተንን መግዛቱን ተከትሎ በፕሪሚየር ሊጉ ከሚሳተፉ 20 ክለቦች ግማሽ ያህሉ በአሜሪካውያን ባለሃብቶች እጅ ገብተዋል።
የመርሲሳይዱ ክለብ ከአውሮፓውያኑ 2016 ጀምሮ የብርታንያ ና ኢራን ጥምር ዜግነት ባላቸው ፋርሃድ ሞሽሪ ባለቤትነት ሲተዳደር መቆየቱ አይዘነጋም።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv












