ክርስትያኖ ሮናልዶ ከአውሮፓውያኑ 2003 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእጩ የባሎንዶር ተሸላሚዎች ዝርዝር ዉጪ ሆኗል።

አዲስ አበባ | ጳጉሜ21 2015| NBC ETHIOPIA -የሽልማቱ አዘጋጅ ፍራንስ ፉትቦል ማጋዚን ለ2023 የባሎንዶር ሽልማት እጩ የሆኑ 30 ተጨዋቾችን ይፋ አድርጓል።
አርጀንቲናዊው የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ሊዮኔል ሜሲ እና ኖርዌያዊው ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ የዝርዝሩ አናት ላይ ተቀምጠዋል።
የሽልማት ስነ- ስርዓቱ የፊታችን ጥቅምት 30 በፈረንሳይ ፓሪስ የሚከናወን ይሆናል።
የአምናው የሦስትዮሽ ባለ ክብር ማንችስተር ሲቲ በርካታ ተጨዋቾችን ለእጩነት በማስመረጥ ቀዳሚው ክለብ ነው።
ከአርሰናል ማርቲን ኦዲጋርድና ቡካዮ ሳካ ተካተዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv










