አዲስ አበባ | ጳጉሜ21 2015| NBC ETHIOPIA -የመስዋዕትነት ቀንን “በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር” በሚል መሪ ቃል ስናከብር የኢትዮጵያ ውድ ልጆች ለከፈሉት እና እየከፈሉት ላለው መስዋዕትነት ክብር በመስጠት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣”ዕለቱን የምናከብረው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገን በመስቀል እና ደም በመለገስ፣ ኢትዮጵያን በመስዋዕትነታቸው ያጸኑ ጀግኖቻችንን በመዘከር እንዲሁም ሀገርና ህዝብን ለመጠበቅ በተጠንቀቅ ከቆሙ የጸጥታ ኃይሎች አባላት ጎን መቆማችንን በማሳየት ነው”ሲሉ ገልጸዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












