አዲስ አበባ | ጳጉሜ 2 2015| NBC ETHIOPIA- አማራ ባንክ ይበልጥ ተደራሽ ለመሆን እና ለደንበኞቹ አማራጮችን ለማስፋት ከበርካታ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ድርጅቶች ጋር በመፈራረም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳውን እያጎላ መሆኑን በጋራ የስምምነት ፊርማው ላይ ተገልጿል።

ከባንኩ ጋር ስምምነት ከተፈራረሙት የቴክኖሎጂ ድርጅቶች መካከል ቡኪንግ ቴክኖሎጂ በሆቴል ኢንደስትሪ ዘርፍ የኦላይን ቡኪንግ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፣ ሌላኛው ቻፓ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ በዲጂታል ግብይት ዘርፍ የተሰማራ የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው።
የዲጂታል ፋይናንሻል ቴክኖሎጂን በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን ተደራሽነት ለማሳደግ የራሱን ድርሻ የሚያበረክት የጋራ ስምምነት ነው አማራ ባንክ ከቴክኖሎጂ ድርጅቶቹ ጋር ያደረገው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv










