በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23/2015፣ NBC ETHIOPIA- ቼልሲ አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ በረጅም የውሰት ውል ስምምነት ሮማን ለመቀላቀል ተቃርቧል።

የጆዜ ሞሪኒሆ ሮማ ፣ ለውሰት ዉሉ 8 ሚሊዮን ፓውንድና የተጨዋቹን ደሞዝ ሙሉ በሙሉ ለመክፈል ተስማምቷል።
የ30 አመቱ ቤልጂየማዊ የ2022/23 የውድድር ዓመትን በኢንተር ሚላን ቤት ማሳለፉ ይታወቃል።
ሉካኩ ከአዲሱ የቼልሲ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ እቅድ ዉጪ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ በድጋሜ ወደ ኢንተር ይመለሳል ተብሎ ቢጠበቅም ሮማን ምርጫው አድርጓል።
ሌላኛው የሴሪ ኤ ክለብ ዩቬንቱስም የተጨዋቹ ፈላጊ እንደነበር አይዘነጋም።
ሉካኩ በ2017 ከኤቨርተን ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ካዘዋወሩት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ ጋር በድጋሜ በሮማ ቤት የሚገናኙ ይሆናል።
በይበልጣል ሰውነት
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc












