በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19/2015፣ NBC ETHIOPIA- የእናቶችና ህጻናት እንዲሁም ለአፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የሚያግዝ የ50 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ከጄኤስአይ ግብረ ሰናይ ድርጅት ተበርክቷል፡፡

ግብረሰናይ ድርጅቱ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በእናቶች እና ህፃናት ጤንነት ላይ ስራዎች ለመስራት ለቀጣይ አምስት አመታት የሚተገበር ፕሮጀክት አቅርቧል፡፡
ፕሮጀክቱ በስድስት የአገሪቷ ክልሎች ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ ፣ ሲዳማ እና ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ያካትታል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ይህ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሲደረግ በአገሪቷ በእናቶች እና በህፃናት እንዲሁም በአፍላ ወጣቶች በጤና አገልግሎት የተሻለ ማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡
ድጋፉ የገንዘብ ብቻ ሳይሆን ፕሮጀክቱ ተፈፃሚ እስኪሆን ድረስ ጄኤስአይ አብሮ ይሰራል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በስድስት ክልሎች ዉስጥ በሚገኙ 67 ወረዳዎች የሚገኙ እናቶች እና ህፃናትን ተደራሽ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












