
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 11/2015፣ NBC ETHIOPIA- ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የቀጣናውን ሰላም የማስከበርና የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ማስረጽ የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት እንደሚሰራባቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ሶስት አመታት የመንግስት የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ዝግጅት ላይ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የዜጎች መብት ማስከበርና የዳያስፖራ ማህበረሰብ ልማትና ሁለንተናዊ ተሳትፎ የማጎልበትና የማሳደግ፣ የፓን አፍሪካኒዝም አስተሳሰብ እንዲጎለብት በ2015 በጀት ዓመት የተከናወኑ ስራዎች ላይ እና በ2016 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር መደረጉም ተገልጿል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc












