
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 11/2015፣ NBC ETHIOPIA -19ኛው የአፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ የሚኒስትሮች መደበኛ ጉባኤ “የአፍሪካን የአካባቢ ችግሮች ለመፍታት ዕድሎችን መጠቀም፣ ትብብርን ማጎልበት” በሚል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደገለጹት፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የአፍሪካ አገራት በጋራ ሊቆሙ ይገባል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ አፍሪካዊያንን ለከፋ ችግር እየዳረጋቸው ይገኛል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በበኩላቸው፣አፍሪካ ለአየር ንብረት ለወጥ አደጋ ተጋላጭ ሆናለች፡፡
አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው በቢሊየን የሚቆጠሩ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር ከ500 ሚሊየን በላይ ችግኞችን መትከሏን ጠቅሰው ለምግብነት ፡ለአካባቢ ጥበቃና ለተለያዩ ተግባራት የሚውሉ መሆናቸውን አስረድተዋል ሲል ኢፕድ በዘገባው ገልጻል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












