
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 11/2015፣ NBC ETHIOPIA-የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የአብሮነት እሴቶችን በማስጠበቅ ለዘላቂ ሰላም ግንባታና አገራዊ ልማት የድርሻቸውን እንዲወጡ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊና የጎንደር ቀጣና ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ ደሳለኝ ጣሰው ጠየቁ።
አጠቃላይ የነበረውን የጸጥታ ችግር በማስመልከት በጎንደር ከተማ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ውይይት ማድረግ ጀምረዋል።
የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩ አቡሀይ በበኩላቸው በነዋሪዎች የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ከተማ አስተዳደሩ በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል ሲል ኢፕድ ገልጿል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












