አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10/2015፣ NBC ETHIOPIA የኒጀር መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ፤ በማሊ ድንበር አቅራቢያ ታጣቂ ቡድኖች ባደረሱት ጥቃት 17 የሚሆኑ ወታደሮች ሲገደሉ ሌሎች 20 የሚሆኑ መቁሰላቸውን አስታውቋል።

እንደ አልጀዚራ ዘገባ ባለፉት አስርት ዓመታት በማእከላዊ ማሊ፣ ሰሜናዊ ቡርኪናፋሶ እና ምዕራባዊ ኒጀር ድንበር አካባቢ የአልቃይዳ እና አይ ኤስ አይ ኤስ አባላት ታጥቀው የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ሆኗል ነው የተባለው ። የኒጀር ጦር መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በመልሶ ማጥቃት እርምጃው ከ100 በላይ የሽብር ቡድኑ አባላት እንደተገደሉ ገልጿል።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc











