

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 09/2015፣ NBC ETHIOPIA – የአድዋ ድልን ታሪካዊ ዳራ መነሻ አድርጐ እየተገነባ የሚገኘው አድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም የኢትዮጵያ ጀግኖችንና የአድዋ መልክዓ ምድርን በሚገልፅ መልኩ ታሪካዊ እሴቱን ጠብቆ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት አስታወቁ።
ሙዚየሙ በከተማችን ውስጥ እስከ ዛሬ ከተገነቡ እና በመገንባት ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች ግዙፉ ሲሆን 11 ብሎኮችን የያዘ 45000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እየተገነባ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች በውስጡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮችን፣ የአድዋ ፈረሰኞች ማስታወሻ፣ ለሴት ጀግኖች ክብር የተሰየመ ማስታወሻ፣ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነፃነት ማስታወሻ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳይ ሙዚየም እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ከ300 እስከ 4000 ሰው ድረስ የሚይዙ የተለያዩ አዳራሾች ይገኙበታል ብለዋል፡፡
ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት የሚደረግ ይሆናልም ሲሉ ተናግረዋል::
መጪውን የአድዋ በዓል የጥቁር ህዝቦች የድል የታሪክ ከፍታን በሚመጥን መልኩ በዚሁ ስፍራ ላይ በጋራ እናከብራለንም ብለዋል በመልዕክታቸው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc










