
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5 2015| NBC ETHIOPIA -የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንሰት ብሩታ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አደርገውላቸዋል ።
የሩዋንዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁን ኢዜአ በዘገባው ገልጿል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












