አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 4 /2015 | NBC ETHIOPIA- በሙሉ ወይም በግማሽ አንስቴዥያ የሚሰሩ የቀዶ ህክምናዎች የስኳር መጠን በማዛባት የስኳር በሽታን ሊያባብሱ ይችላሉ።
???? ከግብ ዉጪ የሆነ የስኳር መጠን ያላቸው ታካሚዎች በቀዶ ህክምና ወቅት ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ ይሆናሉ።

– የስኳር መጠን መጨመር ወይም መቀነስ
– የደም ግፊት መቀነስ
– ከቀዶ ህክምናው በኋላ የቁስል ቶሎ አለመዳን
???? ከቀዶ ህክምና በኋላ ለሚመጡ ኢንፌክሽንዎች መጋለጥ ያመጣል።

– በነዚህም ምክንያቶች ታካሚዎች ለረዥም ጊዜ በሆስፒታሉ ውስጥ እንዲቆዩ ይገደዳሉ።
– ከስኳር በሽታ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች በ አንስቴዥያ ምርጫ ላይ ተፅዕኖ ያደርጋሉ። እነዚህም:-
– የኩላሊት በሽታ
– የልብ በሽታ
– ኒውሮፓቲ
???? ከቀዶ ህክምናው በፊት የሚደረግ ፆም የተላያየ ተፅዕኖ አለዉ:-

– የስኳር መጠን ይወርዳል
– በተለይም ኢንሱሊን የሚወስዱ ታካሚዎች
– በአፍ የሚወሰድ የስኳር መድኃኒት ለመውሰድ ሊያስቸግር ይችላል።
???? በቀዶ ህክምናው ስዓት ላይ ያሉ ችግሮች:-

– በሙሉ አንስቴዥያ ምክንያት የስኳር መጠን ሲበዛ ወይም ሲያንስ የሚመጡ ምልክቶች ይሸፈናሉ
– የስኳር መጠን መጨመር
– የስኳር መጠን ማነስ
???? ከቀዶ ህክምናው በኋላ

– ከአንስቴዥያ ቶሎ አለመንቃት
– የቀዶ ህክምናው ቁስል ቶሎ አለመዳን
– ኢንፌክሽኖችን አለመቋቋም።
???? ስለዚህ ማንኛውም የስኳር ታማሚ ጥብቅ የሆነ የስኳር መጠን ቁጥጥር ያስፈልጋቸዋል
???? ይህን ለማሳካት ታካሚው ሆስፒታል ከገባበት ቀን ጀምሮ ኢንሱሊን በመጠቀም የስኳር መጠን ከግብ ውስጥ ማስገባት (RBS 140-180mg/dl)።
???? የስኳርን መጠን በቅርብ መከታተል።
???? የፆም ሰዓት ለማሳጠር የቀዶ ህክምናውን በጥዋት ማድረግ
???? ከቀዶ ህክምናው በፊት ተገቢውን የሆነ ምርመራ ማድረግ
– ለምሳሌ:- የልብ፣የኩላሊት እና የመሳሰሉት
???? በቀዶ ህክምናው ስዓት በቂ የሆነ የስኳር መጠን ክትትል ማድረግ
– ካነሰ- በደም ስር ግሉኮስ መስጠት
– ከበዛም- ኢንሱሊን መስጠት
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












