በአዲስ አበባ፤ ነሐሴ 3 /2015 | NBC ETHIOPIA-ሱዳን ቀውስ ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ አስታውቋል።

የተፈናቃዮቹ ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር በመላ ሀገሪቱ የጤና ሁኔታ እየተባባሰ መጥቷል ሲል የኤጀንሲው ባልደረባ ዊሊያም ስፒንድለር በጄኔቫ በተደረገው የተባበሩት መንግስታት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።
በነጭ አባይ ግዛት በ10ቱም የስደተኞ ካምፖች የጤና እና የስነ ምግብ አገልግሎት ፣አስፈላጊ መድሃኒቶች፣ ሰራተኞች እና አቅርቦቶች እጥረት ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድተዋል ያሉት ሚኒስትሩ ከ144,000 በላይ አዲስ ተፈናቃዮች ካርቱም መግባታቸውን ጠቁመዋል።
ስፒንድለር በአጠቃላይ የተፈናቀሉት ግለሰቦች ቁጥር 700,000 ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ጎረቤት ሀገራት የተሰደዱ ሲሆን 195,000 ደቡብ ሱዳናውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተገደዱ መሆናቸው ተገልጿል።

በሱዳን ውስጥ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ እነዚህም 187,000 ስደተኞች በቀውሱ መጀመሪያ ላይ በሀገሪቱ ይኖሩ እንደነበር ገልጿል።
ከግንቦት 15 እስከ ሀምሌ 17 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ300 በላይ የሚሆኑ በተለይም ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናት በኩፍኝ እና በተመጣጠነ ምግብ እጥረት መሞታቸው ታዉቋል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc










