
አምባሳደር ምስጋኑ በውይይቱ ወቅት የአዘርባጃን መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ በትብብር ለመስራት ያለውን ፍላጎት አድንቀዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ ኢትዮጵያ አዘርባጃን በፌደራል እና ክልል የአስተዳደር እርከኖች ካደረገቻቸው ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎች ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ አመልክተዋል።
የአዘርባጃን የፐብሊክ ሰርቪስና ሶሻል ኢኖቬሽን ሚኒስትር ኡልቪ ሜዲዬቭ በበኩላቸው የአገራቸው መንግስት የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ጨምሮ አገራቱ የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ የልማት እርዳታ፣ትምህርት፣ባህል እና ቱሪዝም መስኮች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር እንደምትፈልግ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












