አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 20/2015 NBC Ethiopia- የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ የ2016 በጀት አመት የእቅድ ስትራቴጂን በተመለከተ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ኢትዩ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 90 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለማግኘት ማቀዱን አሳውቀዋል።
ተቋሙ በቀጣዩ በጀት ዓመት የገበያ ድርሻውን በማስፋት የደንበኞችን ፍላጎት በይበልጥ ለማርካት በእቅድ ተይዞ በትኩረት እንደሚሰራበት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።
የቴሌኮም ኔትወርክን በማስፋት የ4ጂ / አድቫንስድ 4ጂ፣ 3ጂ ኔትወርክ፣ የ 5ጂ ኔትወርክ ማስፋፊያ ን በማከናወን የሞባየል ኔትወርክ ደንበኛ የማስተናገድ አቅምን 92 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱም ተገልጿል።

በተጨማሪም 2016 በጀት ዓመት የደንበኞችን ብዛት በ 8 ነጥብ 3 በመቶ በማሳደግ 78 ሚሊየን ለማድረስ እንደሚሰራም ገልጿል።
ተቋሙ የሞባየል ጣቢያዎቹን በገጠር አካባቢዎችም በማስፋት ፣ አማራጭ የሀይል አቅርቦት በማቅረብና ለበርካቶች የስራ እድል የሚፈጥሩ ተግባራትን በመከወን እንዲሁም ዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑን ለማፋጠን ፥በርካታ ስራዎችን በመስራት ፤ውጤታማ ተግባራትን ለማከናወን በትኩረት እንደሚራ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ አብራርተዋል።
በሰላማዊትወንድወሰን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc










