
አዲስ አበባ ሐምሌ 5 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- አቶ ደመቀ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ውይይታቸው በሁለትዮሽና በወቅታዊው የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ እየተሻሻለ የመጣውን የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ትብብር በተፋጠነና በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን እንደሚገባው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጸዋል።
ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ኢጋድ በአዲስ አበባ ያደረገውን ውይይት ኢትዮጵያ በማስተናገዷ አመስግነው የሱዳን ኃይሎች የተኩስ አቁም በማድረግ ለችግሩ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ እና ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia












