
አዲስ አበባ ሐምሌ 5 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- ከዮርዳኖስ መንግስት ጋር በዮርዳኖስ ለስራ የሚሰማሩ ኢትዮጵያውያንን መብትና ጥቅም የሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ምክክር በማካሄድ ስምምነት መፈራረማቸውን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል አስታውቀዋል፡፡
የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት 33 ሺህ ኢትዮያውያን በሚገኙባት ወደ 33,000 ኢትዮያውያን በሚገኙባት ዮርዳኖስ የአለም አቀፉን የስራ ድርጅት የሰራተኛና አሰሪ ግንኙነት መስፈርቶች ጨምሮ የደመወዝ ጭማሪ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ ከባቢ፣ ህክምናና ኢንሹራንስን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የሁለቱ ሀገራት ተደራዳሪ ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ላይ ከዮርዳኖስ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ሰራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር ሚ/ር ዮሴፍ ሻማሊ ጋር ስምምነት ላይ ደርሰናል።

በየጊዜው የሚከሰቱ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት በሁለቱ ሀገራት መካከል በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ተመስርቶ ክትትል የሚደረግበትና የሚታደስ ይሆናል ሲሉም ነው ሚኒስትሯ ያነሱት፡፡
ስምምነቱ ከስራ ስምሪት ግንኙነት ባሻገር ኢትዮጵያ ከዮርዳኖስ መንግስትና ህዝብ ጋር ያላትን የቆየ በእህትማማችነት ላይ የተመሰረተ የዲፕሎማሲ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና ትብብር የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል ሲል ኢ ፕ ድ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia












