
በአውስትራሊያ በተደረገው የሴቶች የዓለም ሀገር አቋራጭ የ10 ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮዮጵያዊቷ አትሌት ፅጌ ገብረ ሰላማ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች።
ኢትዮዮጵያዊቷ አትሌት ፅጌ ገብረ ሰላማ ርቀቱን 33:56 በማጠናቀቅ ኬንያዊቷን አትሌት ቤትሪስ ቺቤት ተከትላ መግባት ችላለች።
በርቀቱ የተሳተፈችው የ 10,000 ሜትር የዓለም ሻምፒዮኗ ኢትዮጵያዊት አትሌት ለተሰንበት ግደይ አራተኛ በመውጣት ውድድሯን አጠናቃለች።

የወንዶች በተደረገው የዓለም የሀገር አቋራጭ የ10 ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮዮጵያዊው አትሌት በሪሁ አረጋዊ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችሏል።
ዩጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ ርቀቱን በበላይነት ሲያጠናቅቅ ኢትዮዮጵያዊው አትሌት በሪሁ አረጋዊ 29:26 በመግባት ውድድሩን ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።
በርቀቱ የተሳተፉት ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሀይለማርያም አማረ ፣ ሞገስ ቱማይ ፣ ጭምዴሳ ደበሌ እና ሰለሞን ባረጋ ከ9-12 ያለውን ደረጃ በመያዝ ተከታትለው መግባት ችለዋል
ሃና ተሰማ
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት









