ልክ በዛሬዋ ቀን ሀምሌ 22 1928 ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በፋሽስት ጣሊያን ጦር የተረሸኑበት ቀን ነው፡፡
የጣሊያን ጦር ኢትዮጵያን 1928 ዓ.ም በወረረበት ወቅት፤ የኢትዮጵ ሕዝብ ለወራሪው ጠላት እንዳይገዙ በማውገዛቸው ሕዝቡ የሀገሩንና የቤተክርስቲያንን ልዕልና ለማስጠበቅ ነቅቶ እንዲታገል በማስተማራቸው፣ በማበረታታቸው፣ በማጽናናታቸው የፋሺስት ጣልያን ወታደሮች ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን አስረው ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም በአደባባይ በጥይት ገድሏቸው፡፡
በወቅቱ የጣልያን ጦር አዛዦች አቡነ ጴጥሮስን ለማባበል ብዙ ጥረት አድርገዋል፡፡ የፋሽስት ጣልያንን አገዛዝ ተቀብለው ሕዝቡን እንዳይቀሰቅሱ ፣ እንዳያስተምሩ፣ ለሃገሩ ክብርና ለቤተክርስቲያን ልዕልና እንዳይታገል እንዲያደርጉ ለመደለል የሥልጣን ሃብትና ንብረት ገፀ በረከት አቅርበውላቸውም ነበር፡፡
ነገር ግን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ አልተቀበሉም፤ ይልቅም የኢትዮጵያን ህዝብ ባርከው ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡
በ-ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












