፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 04 2016| NBC ETHIOPIA- ከቅርብ አመታት ወዲህ በአለማችን የሚገኙ ትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ፊታቸውን ወደ ኤሌክትሪክ መኪና ማምረት እያዞሩ ነው፡፡የቻይና ኩባንያዎችም የዓለም ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ገበያን በስፋት መቆጣጠር ጀምረዋል፡፡
ከቻይና የሚላኩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ምርቶች ትልቁ ተቀባይ የአውሮፓ ህብረት ሲሆን 40 በመቶ የሚሆነውን ይይዛል። ይህም የቻይና ምርቶች የአውሮፓን ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ገበያን በስፋት እንዲቆጣጠሩ አስችላቸዋል፡፡
የአውሮፓ መንግስታት በቻይና ምርቶች በላይነት የተያዘውን የአውሮፓ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ገበያን ለመፎካከር የሚያስችላቸውን አቅም ለመገንባት እየሠሩ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የአውሮፓ ሀገራት በቻይና ምርቶች የተጥለቀለቀውን የአህጉሪቱን ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ገበያ ለመፎካከር የሚያስችሉ አዳዲስ ኢንቬስትመንት ለመሳብ ፤ማኑፋክቸሪንግ ለመመገንት እና የስራ ድርሻ ለማግኘት ብርቱ ፉክክር እያደረጉ መሆኑም ነው የተገለፀው፡፡የሚታየውን ተመጣጣኝ ያልሆነ የገበያ የበላይነትን ለመቀነስ የአውሮፓ ህብረት በቻይናን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ምርቶች ላይ የታሪፍ ዋጋን ይፋ ሊያደርግ መሆኑን ገልፃል፡፡

ዋሽንግተን ለቻይና ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ምርቶች ታክስ በአራት እጥፍ ካሳደገች ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ብራስልስ ከቻይና አምራቾች በሚገቡ ምርቶች ላይ አዲስ ታሪፍ ሊጥሉ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡ እንዲሁም እንደ ቴስላ ያሉ የምዕራባውያን አምራቾች ከቻይና ወደ አውሮፓ የሚላኩ መኪናዎችን አዲስ ታሪፍ ይፋ ይሆናል ተብሏል፡፡
እርምጃው የመጣው የአውሮፓ አውቶሞቢሎች ከቻይና ባላንጣዎች በርካሽ ዋጋ እየጎረፉ በመሆናቸው ተከትሎ ነው፡፡
በተለይም የጀርመን አውቶሞቢሎች በቻይና ሽያጭ ላይ በጣም ጥገኛ መሆናቸው ተመጣጣኝ ገበያ እንዳይኖር ማድረጉም ተገልጿል፡፡
ህብረቱ በቻይና የመኪና ምርቶች ላይ ታሪፍ በመጨመር ግብር ለመሰብሰብ ቢያስብም አባል ሀገራቱ አዳዲስ ፋብሪካዎችን ለመገንባት የሚፈልጉ ቻይናውያንን ለመሳብ በሚያደርጉት ሂደት የራሳቸውን ፋብሪዎች ለመገንባት የሚያደርጉትን ሙከራ እያደናቀፉ መሆኑን ህብረቱ ባወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡
ቻይና የኤሌክትሪክ መኪና አምራች የሆኑት ቢ ዋይ ዲ፣ ቼሪ አውቶሞቢል እና በመንግስት ባለቤትነት የተያዘው SAIC ሞተርን ጨምሮ በሀገራቸው ውስጥ ለማምረቻ የሚያወጡት ወጪ ዝቅተኛ ቢሆንም በአውሮፓ የምርት ስያሜዎቻቸውን ለመገንባት እና ብዙ ትርፍ ለማግኘት ይፈልጋሉ ሲሉ በባይን አማካሪ ኩባንያ አጋር ጂያንሉካ ዲ ሎሬቶ ገልጸዋል ፡፡ አክለውም በቀጣይ የቻይናውያን አውቶሞቢሎች በአውሮፓ ደንበኞች መካከል ፍላጎት እንዲኖራቸው ከፈለጉ መኪኖቻቸው በአውሮፓ ውስጥ ማምረት አለባቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በቻይና ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ለመጣል ያቀደውን ታሪፍ በዚህ ሳምንት ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የሚጣለው ታሪፍ በአንድ በኩል፣ የአውሮፓ አውቶሞቢሎች ከቻይና አቻዎቻቸው ጋር በተሻለ ሁኔታ እንዲወዳደሩ ሊረዳቸው ይችላል የተባለ ሲሆን ነገር ግን በከፍተኛ ሁኔታ ኢንቨስት በማድረግ ላይ በሚገኙ የቻይና አውቶሞቢል ኩባንያዎች በአውሮፓ ገበያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ የበላይነቱን ተቆጣጥረው ሊቆዩ ይችላሉ ሲሉ ባለሙያዎች በመግለፅ ላይ ናቸው። ህብረቱ ሊጥል ስላሰበው የታሪፍ መጠን ያለው ነገር ባይኖርም ተንታኞች ከ10 በመቶ እስከ 25 መቶ ታሪፍ ሊጣል ይችላል ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
የቻይና ምርት ስም ያላቸው መኪኖች ሽያጭ ባለፈው አመት 4 በመቶ የአውሮፓ ገበያን የያዘ ሲሆን በ2028 7 በመቶ እንደሚደርስ ባሉያዎች ትንበያቸውን አስቀምጠዋል፡፡
የአውሮፓ ሀገራት የቻይና ኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመፎካካር የሚያስችላውን አዳዲስ ማምረቻዎች ለመክፈት በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን የአውሮፓ ህብረት አስታውቋል፡፡እ.ኤ.አ. በ2023 ወደ 500,000 የሚጠጉ ተሽከርካሪዎችን ያመረተችው ሃንጋሪ የመጀመሪያውን የአውሮፓ ፋብሪካ ኢንቬስትመንት ያገኘችው በቻይና ኩባንያ ሲሆን ባለፈው አመት ቢአይዲ ኤሌክትሪክ መኪና ማምረት ጀምራለች፡፡ በ2025 የአውሮፓ ፋብሪካን በሁለተኛነት ለመምራት አቅጃለሁ ብላለች፡፡ ሀንጋሪ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አዳዲስ የባትሪ ፋብሪካዎችን ለመገንባት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጓል በአሁኑ ጊዜ ከ 10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንቶችን የሚደግፉ በርካታ መርሃ ግብሮች እንዳሏት የሀገሪቱ ልማት እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለሮይተርስ ተናግሯል፡፡
ከጀርመን ቀጥሎ ሁለተኛዋ የአውሮፓ ትልቁ መኪና አምራች አገር የሆነችው ስፔን የቻይና አምራቾች በሀገሪቱ እንዲቋቋሙ እየሰራች መሆኑን አስታውቋለች፡፡እ.ኤ.አ በ2023 ቻይና ከ4 ሚሊዮን በላይ መኪኖችን ወደ ውጭ የላከች ሲሆን ይህም በዓለም ላይ ትልቁን የመኪላ ላኪ ያደረጋት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 1.2 ሚሊዮን የኤሌክትሪክ ተሸከርካራች ነበሩ። የቻይናው ቢ ዋይ ዲ ኩባንያ የዓለማችን ቁጥር አንድ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሻጭ መሆኑን ከወራት በፊት መገለፁ ይታወሳል፡፡












