አዲስ አበባ | መስከረም 30 2016| NBC ETHIOPIA – ➡️ የልጆች ስክሪን ጊዜ ወይም የቲቪ መመልከቻ ገደቦች
በዚህ ዘመን ልጆች የስክሪን ጊዜያቸውን ወይም ቲቪ ፣ ሞባይል እና ታብሌቶችን በመመልከት ላይ ናቸው ከ2 አመት በታች ያሉት ህፃናት እንኳን አሁን ከሚመከረው የጊዜ መጠን በላይ ነው የሚመለለከቱት።

➡️ ቤተሰብ ምን ማወቅ አለበት?
ዕድሜያቸው ከ 2 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት የስክሪን ጊዜን ሙሉ በሙሉ እንዳይጠቀሙ ማድረግ፣ ከ 2 እስከ 5 ዓመት እድሜ ያላቸው ህጻናት ግን በቀን ከ 1 ሰዓት የማይበልጥ እንዳይጠቀሙ መከልከል።

➡️ እነዚህ መመሪያዎች በዓለም ዙሪያ የወጡ ቢሆንም ኢትዮጵያን ጨምሮ መመሪያዎቹን በማክበር ረገድ ትልቅ ክፍተት ስላለ ለህብረተሰብ ማሳወቅ አስፈላጊ ነው።
1. ከሁለት ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የስክሪን ጊዜን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት
2. በትናንሽ ልጆች ከፍተኛ ደረጃ የስክሪን አጠቃቀም ከእድገታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ጋር ሊዛመድ ይችላል
3. ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት በጣም የዲጂታል ሚዲያ ተጠቃሚዎች ስለሆኑ በቤተሰብ ቁጥጥር ውስጥ መሆን ይኖርበታል።
4. የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ (AAP) እና WHO ዕድሜያቸው ከ 2 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት (ከቪዲዮ ቻት ውጭ) የስክሪን ጊዜ እንዳይወስዱ እና ዕድሜያቸው ከ 2 እስከ 5 ዓመት ለሆኑ ሕፃናት በቀን 1 ሰዓት እንዲቆይ መክረዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












